ቤተሰብ - ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ማህበር በላይፕዚግ
BETESEB - Ethiopian and Friends of Ethiopia Community, Leipzig
[Abbrechen]
ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሰን፤ አደረሳችሁ።
መልካም የከተራና የጥምቀት በዓል!
በዩክሬን ጦርነት ምክንያት የነዳጅ እና የናፍታ ዋጋ በጣም ሰለጨመረ የጀርመን ፌደራል መንግስት በ 9-ዩሮ ትኬት ዜጎችን መደገፍ እና ዜጎች ከመኪና ወደ ህዝብ ትራንስፖርት መቀየርን ቀላል ማድረግ ይፈልጋል። በዚህ ትኬት 9€ ከፍለው ለአንድ ወር በመላው ጀርመን መጓዝ ይችላሉ።
- ትኬቱ መቼ አና የት ነው የሚገኘው?
ትኬቱን 23. Mai 2022 ጀምሮ፣ በድህረ ገጽ bahn.de፣ በስልክ App DB Navigator፣ በትኬት መሸጫ ማሽኖች እና በባቡር ጣቢያዎች (Bahnhof) ውስጥ ያሉ ትኬት መሸጫ ቦታዎች መግዛት ይችላሉ።
- ትኬቱ የሚሰራው ለምን ያህል ጊዜ ነው?
የ9-ዩሮ ትኬቱ የሚሰራው ከ Juni 1.2022 እስከ August 31.2022 ነው።
ትኬቱ የሚያገለግለው ለአንድ የቀን መቁጠሪያ ወር ሲሆን፣ ከወሩ መጀመሪያ ቀን (0፡00 ሰአት) እስከ ወሩ መጨረሻው (24፡00 ሰአት) ነው። ማለትም ከ Juni 1 እስከ 30፣ ከ July 1 እስከ 31 እና ከ August 1 እስከ 31 ነው።
- ትኬቱ በየወሩ አዲስ መግዛት አለበት?
አዎ፣ ምክንያቱም የ9-ዩሮ ትኬቱ የሚሰራው ለአንድ ወር ብቻ፣ ከወሩ መጀመሪያ እስከ ወሩ መጨረሻ ስለሆነ ለእያንዳንዱ ወር አዲስ መግዛት አለበት።
- ትኬቱ የትላይ ነው የሚሰራው?
የ9-ዩሮ ትኬቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም መንገዶች እና በሁሉም የአከባቢ የህዝብ ማመላለሻ መንገዶች (ÖPNV) ለማንኛውም ጉዞዎች አገልግሎት ላይ ሊውል ይችላል። እነዚህም የሚከተሉትን ያካትታሉ፤
- አውቶቡስ
- S-Bahn እና U-Bahn
- ትራሞች (Straßenbahnen)
- የክልል ባቡሮች (Regionalbahnen)
- ክልላዊ ኤክስፕረስ (Regionalexpress)
ትኬቱ በረጅም ርቀት ባቡሮች (ለምሳሌ IC፣ EC፣ ICE) እና የረዥም ርቀት አውቶቡሶች ላይ አይሰራም።
- የዓመት ወይም የወር ትኬት ያላቸው የ9-ዩሮ ቲኬት መግዛት አለባቸው?
የዓመት ወይም የወር ትኬት ያላቸው ምንም እርምጃ መውሰድ የለባቸውም። የአመታዊ ወይም የወርሃዊ ትኬት ደንበኞች ትኬቱን ከገዙበት ድርጅት ስለ ክፍያው አውራረድ (የቀጥታ ክፍያ ቅነሳ ወይም ክፍያ መመለስ) ይነገራቸዋል።
- ልጆች በነጻ መጓዝ ይችላሉ?
ከ 6 አመት በታች የሆኑ ህጻናት በነጻ ይጓዛሉ። ቲኬት አያስፈልጋቸውም።
ከ6-14 አመት እድሜ ያላቸው ልጆች የራሳቸው ቲኬት ወይም የ9-ዩሮ ቲኬት ያስፈልጋቸዋል፣ በነጻ ሊወሰዱ አይችሉም።
- ብስክሌቶችን በነጻ መውሰድ ይቻላል?
ብስክሌት መውሰድ በ9-ዩሮ ቲኬት ውስጥ አይካተትም።
- ትኬቱ ለ1ኛ ደርጃ መቀመጫም ይሰራል?
አይሰራም። የ9-ዩሮ ትኬቱ የሚሰራው ለ2ኛ ደረጃ መቀመጫ ብቻ ነው።
- ትኬቱን ማን መግዛት ይችላል?
ማንም ሰው ትኬቱን መግዛት ይችላል። ገደብ የለም።
- ትኬቱ ለFlixtrain እና Flixbus ይሰራል?
አይሰራም። ምክንያቱም የFlixtrain እና Flixbus አገልግሎቶች የረዥም ርቀት ባቡሮች እና የረጅም ርቀት አውቶቡሶች ስለሆኑ፣ የረጅም ርቀት ትራንስፖርት ደግሞ በ9-ዩሮ ትኬት ውስጥ አይካተትም።
«wenigerየተከበራችሁ የእስልምና ኃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ፥
እንኳን ለ1443ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን እያልን በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር አና የአብሮንት እንዲሆን እንመኛለን።
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኩዋን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን እያልን: በአሉ የሰላም የፍቅር የደስታ እና የአንድነት ይሆን ዘንድ እንመኛለን!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ልጆቹዋን ይባርክ!
መልካም አዲስ አመት!!
Gesundes Neues Jahr!!
Happy new year!!
እንኩዋን ለ 2022 አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።
አመቱ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር እና የመተሳስብ ይሁንልን። አሜን!
ለመላው የሙስሊም እምነት ተከታዮች እንኳን ለመውሊድ በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን::
በአሉ የሰላም የጤና፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።
እንኳን ለመስቀል ደመራ በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን::
በአሉ የሰላም: የአንድነት እና የመተሳሰብ ያድርግልን ዘንድ ከልብ እንመኛለን::
በአሉ ስናከብር በሃዘን ውስጥያሉ : በችግር ላይ የወደቁ ዜጎቻችንንእያሰብን ለሃገራችን እና ለሃገራችን ህዝብ ሁሉ ዘላቂ ስላም እንዲሰጠን ፈጣሪያችንን እየተማፀንን እንዲሁም አደራ እንላለን::
ለመላው እስልምና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለ1442ኛው አመት ሒጅራ የኢድ አል-አዳሐ (አረፋ) በአል በሰላም አደረሳችሁ፣አደረሰን።
በአሉ የሰላም፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ ከልብ እንመኛለን።
ለመላው እስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ ለ 1442 ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
እያልን መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን።
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ እንዲሁም የአብሮነር ያርግልን።
መልካም ኢድ አልፈጥር!
ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያን አና የኢትዮጵያ ወዳጆች፣ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን፤
እንኳዋን ለብርሃነ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን እያልን
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር አና የአብሮንት እንዲሆን እንመኛለን።
ከነገ 24.04.2021 ጀምሮ በአዲሱ የኮሮና መከላከያ ደንብ (Bundes-Notbremse) መሰረት Sachsen ውስጥ የኮሮና የቁጥጥር እርምጃ ስራ ላይ ይውላል፣ በላይፕዚሽም እንዲሁ።
ከመቶ ሺህ ስንት አዲስ ኢንፌክሽን (Infektion) በሰባት ቀን ውስጥ እንዳለ የሚያሳየውን (Incidenz) ተከትሎ ህጎቹ ይጠብቃሉ ወይም ይላላሉ።
ዛሬ 23.04.2021 ላይፕዚግ ኢንሲደንዙ 121,9 ነው። ስለዚህ ከነገ 24.04.2021 ጀምሮ፤
- መገናኘት የሚቻለው ከራስ ቤተሰብ ሌላ ከአንድ ሰው ጋር ብቻ ነው (ልጆች እስከ 14 አመት ድረስ አይቆጠሩም)
- ከለሊቱ አራት ሰአት እስከ ንጋቱ 11 ሰአት (22-5 Uhr) ለስራ ምክንያት ካልሆነ ቤት ለቆ መውጣት አይፈቀድም
- ለህይወት በጣም ከሚያስፈልጉ ነገሮች በቀር (Grundversorgung) ኢንሲደንዙ 150 እስኪሞላ ድረስ ሌሎች ሱቆችም በ click and meet ማለትም Einkaufen mit Termin ማለትም ግዢ በቀጠሮ ይቻላል።ለዚህ ግን ወቅታዊ የሆነ ይኮሮና ኔጋቲቭ ቴስት ያስፈልጋል። ቴስቱንም ለሁሉም ዜጋ በሳምንት አንዴ በነጻ በተለያየ Testzentren ለምሳሌ ባንሆፍ ውስጥ ማሰራት ይቻላል። ሚያገለግለው ለ24 ሰአት ነው።
- ት/ቤት በ Wechselmodell ማለትም ተከፋፍሎ ይከፈታል። ሆኖም ኢንሲደንዙ ከ 165 ካለፈ ት/ቤቶችም ይዘጋሉ። በተረፈ ሌላው ባለበት ይቀጥላል።
ስለዚህ ኢንሲደንሱን በየጊዜው መከታተል ጠቃሚ ነው።
እንኳን ለገና በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ እያልን፤
ለበዓሉ ጊዜ ብሎም በቀጣይነት ለሁላችንም በያለንብት እንዲሁም ለሃገራችን ሰላም፣ ጤንነት፣ ፍቅር እና አብሮነትን እንመኛለን።
መልካም ገናፈጣሪ ሃገራችንን ይጠብቅልን!እንኳን ለጎርጎሮሳውያኑ 2021 ዓ/ም በሰላምና በጤና ጠብቆ አደረሳችሁ አደረሰን እያልን:
ዓመቱ የሰላም: የጤና: የስኬት እንዲሁም ዓለማችን ከኮሮና ነፃ ሆና ጤንነት ሰፍኖ ወደ ቀድሞ ኑሯችን የምንመለስበት: ሀገራችንም ሰላሟ ሰፍኖ ህዝቦቿ በሰላም ወተው የሚገቡበት: ሰብሎቿ አምረው አውድማ ጎተራዋን ሞልቶ: ረሀብ እና መፈናቀል ቀርቶ የጥጋብ እና የተትረፈረፈ የምርት ዘመን ይሁን በማለት መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን::
መልካም አዲስ ዓመት 🍾
ከ Noverber 2 2020 ጀምሮ ተጨማሪ የኮሮና ደንቦች በመላው ጀርመን ይተገበራሉ፤
- አደባባይም ሆነ በቤት ውስጥ የሁለት ቤተሰብ አባላቶች ብቻ፣ በቁጥር 10 የማይበልጡ መገናኘት ይችላሉ። ቤት ውስጥ ፓርቲ ማድረግ አይፈቀድም።
- ምግብ ቤቶች፣ቡና ቤቶች፣ክለቦች፣ዲስኮዎች፣መጠጥቤቶች እና መሰል ተቋማት ይዘጋሉ። ወደ ቤት ይዞ ሚኬድ ምግብ ግን መሸጥ ይችላል።
- ሱቆች አና ገበያዎች ክፍት ሆኖ ይቀጥላል። ውስጥ ግን በ 10 ካሬ ሜትር የሽያጭ ቦታ ከአንድ ደንበኛ በላይ አለመኖሩን መረጋገጥ አለበት።
- ትምህርት ቤቶች እና መዋእለ ህጻናት ክፍት ሆነው ይቀራሉ።
- ሆቴሎች እና ማደሪያ ቤቶች ለጊዜው ምንም የቱሪስትማረፊያ አይሰጥም። ዜጎች ከግል ጉዞዎች፣ ከቀን ጉዞዎች እና ከዘመዶች ጉብኝቶች መቆጠብ አለባቸው።
- መዝናኛ ቤቶች እንደ ፊልም፣ ቲያትር፣ ኦፔራ እና ኮንሰርት ቤቶች እና መሰል ተቋማት ይዘጋሉ።
- ስፖርት እና መዋኛ ቤቶች ይዘጋሉ። የግል ስፖርት ለሁለት ወይም ከቤተሰብ አባልጋር ይቻላል። የፕሮፊ የስፖርት እንደ ቡንደስሊጋ አይነት ያለ ተመልካቾች ሊከናወኑ ይችላሉ።
- የቆንጅና ሳሎኖች፣ ማሳጀ ቤቶት፣ ንቅሳት ስቱዲዮዎች እና የመሳሰሉት ይዘጋሉ።
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ወንድም እህቶቻችን በሙሉ፤
እንኩዋን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!🙏🏽
በአሉ የሰላም፣ የጤና፣ የደስታ፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ እና የመቻቻል እንዲሆንልን እንመኛለን። ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንን ሰላም ያርግልን፣ ይጠብቅልን።
መልካም በአል🙏🏽
መልካም አዲስ አመት!
የጎመን ምንቸት ውጣ የስጋ ምንቸት ግባ!
2013 የሰላም፣ የጤና፣ የአንድነት፣ የብልፅግ እና የስኬት እንዲሁም የፍቅር ዘመን እንዲሆንልን ስንል እንመኛለን።
ባለፈው አመት በቆሰልንባቸው፣ ባዘንባቸው ሁሉ የምናገግም፣ አገራችን የሰላም አየር የምትተነፍስበት፣ ለእርቅ፣ ለውይይት የምንቀመጥበት፣ የስራ፣ የእድሳት አመት ይሁንልን።
እዚህ ያደረሰን ፈጣሪያችን ክብር ምስጋና ይግባውና በአዲሱ አመት ይህንን ክፉ ጊዜ ከቁጥር ሳያጎለን አሻግሮ እንደዚህ ለመሰባሰብ ያብቃን!!
መልካም አዲስ አመት ለሁላችን።
የተወደዳችሁ የቤተሰብ አባሎች
የዘመን መለወጫ እንቁጣጣሽ በአልን አንድ ላይ እንደ ቤተሰብ ከሌላው ጊዜ በተለየ በሃገራችን ወግ እና ደንብ አብረን ለማክበር ቅድመ ዝግጅቶችን ከማከናወን ባሻገር ቦታውንም መርጠን የግብዣ ጥሪ ለመላክ በምንሰናዳበት በዚህ ወቅት በተለያዩ የጀርመን ክልሎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያሻቀበ የመጣው የ COVID19 አዲስ የተያዙ በሽተኞች ቁጥር ነገሩን ረጋ ብለን እንድናስታውል ግድ ብሎናል።
በዚህም መሰረት ለጊዜያዊ ደስታ ስንል የምንወዳቸውን የቤተስብ አብሎቻችን እና ቤተስቦቻቸውን ለዚህ አደጋ ከምናጋልጥ የበአሉን ዝግጅት ላልተወሰነ ጊዜ ማስተላለፉ ይሻላል በሚል ውሳኔ ስለተስማማን፣ ምንም እንኳን ልባችን ቢያዝንም ከራሳችን እና ከልጆቻችን ጤንነት የሚበልጥ ነገር ስለሌለ ሁኔታው ሲረጋጋ በተሻለና በሚያስጎመጅ መልኩ እንደምናከብር ከወዲሁ ቃል እንገባለን።
ሰላምና ጤና ለሁላችን! ሃገራችንን ፈጣሪ ይጠብቅልን!
የቤተሰብ ቦርድ
የተወደዳችሁ የ ቤተሰብ አባሎችና ወዳጆች፣
የነገውን የ Leipziger Zoo ጉብኝት ፕሮግራም ግብዣን ጥሪ ተከትላችሁ ክልጆቻችሁ ጋር ወይም ከልጆቻችሁ ጎዋደኞች ጋር ለመምጣት በመወሰናችሁ የሚሰማንን ደስታ በማህበራችን ስም እየገለጽን ይህ ቀን ለሁላችንም በተለይ ለልጆቻችን የማይረሳ ክስተት እንዲሆን የሚከተለውን የጊዜ ሰሌዳ አዋቅረናል።
እዚህ ላይ በጣም ለማሳሰብ የምንፈልገው ነገር ቢኖር የቀጠሮ ሰአታችንን በማክበር እንድትተባበሩን ስንል በትህትና እንጠይቃለን።
በተለይም መጀመሪያ ስንገናኝ፤
- ከጧቱ 9 ሰአት እስከ 9 ተኩል(9:00-9:30) ላይፕዚግ ሃውፕት ባንሆፍ (Hauptbahnhof) ውስጥ ያለው Starbucks Coffee ፊት ለፊት እንዲገኙልን ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን።
- ከአጭር ትውውቅ በህዋላ ከልጆቹ ጋር ወደ Zoo የእግር ጉዞ እናደርጋለን። እዚህ ላይ የልጆቹን መግቢያ ቲኬት በግሩፕ ስለምንቆርጥ ሁሉም በተባለው ሰአት መገኘት እንዳለባቸው በድጋሚ ለማሳወቅ እንወዳለን።
- አዋቂዎች እና ወላጆች ካስፈልገ ከኛ ጋር ወይም በግል ቀደም ብለው ቲከቱን ለመቁረጥ ወደ ስፍራው ማምራት ይችላሉ።
- ከገባን በህዋላ በቦታው በምናወጣው ፕላን መሰረት የእለቱን ውሎዋችንን የምናካትት ይሆናል። ከወዲሁ ሁሉንም ማቀድ ችግር ሊሆን የሚችልበት ምክንያቶች ለምሳሌ እንደ ሌሎች ጎብኚዎች ብዛት፣ እንደ አየሩ ሁኔታ (በጣም ሞቃት) እና የመሳሰሉት ምክንያቶች በመኖራቸው ለኛም ለልጆቻችንም የሚመቸንን እቅድ አውጥተን እንደ ቤተሰብ ተደስተን እንደምንውል ጽኑ እምነታችንና ምኞታችን ነው።
በአሁኑ ፕሮግራም ለመሳተፍ ያልተመቻችሁ (ያልሰማችሁ) አባሎች ካላችሁ ምንም የመቆጨት አይነት ስሚት እንዲሰማችሁ አያስፈልግም። ምክንያቱም ይኼ የመጀመሪያችን እንጂ የመጨረሻችን ባለመሆኑ! ይህንንም በተመለከተ ከናንተም ለሚመነጩ ሃስቦች አድንቆታችንን እንገልጻለን።
በመጨረሻም ለልጆቹ የሚሆን መጠጥ ውሃ ጭማቂ (saft) እንዲሁም የሚበላ ነገር ይዛችሁ ብትመጡ ተመራጭ ይሆናለ ብለን እናስባለነ።
የ ቤተሰብ ቦርድ አባሎች
«wenigerየምስራች ለልጆች!
ውድ እና የተከበራችሁ የበተሰብ ማህበር አባሎች እንደምን ከረማችሁ!
የበጋን በአላት (Sommerferien) ምክያት በማረግ በተስብ - ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ማህበር ይህንን እድል ሲያመቻችልዎ ከልብ በመነጨ ደስታ ነው። እናም ለልጆችዎ የሚሆን የጉብኝት ፕሮግራም አመቻችትዎልዎታል።
ይህም ፕሮግራም የ ZOO ጉብኝትን የሚመለከት ሲሆን ከታች በተጠቀሰው ቀን የልጆችን የመግቢያ ዋጋ ማህበራችን ለዚህ ማስፈጸሚያ ባገኘው ድጎማ ወይም “ስፖንሰር” ሚሸፍን መሆኑን እየገለጽን፣ ልጅዎት(ችዎ) የጉብኝቱ ታዳሚ እንዲሆኑ ስንል በትህትና እንጠይቃለን። እርስዎም ለመሳተፍ ከፈለጉ ቲኬትዎን ገዝተው እንደ ቤተስብ እለቱን አብረን እንድናሳልፍ ጋብዘንዎታል።
ከሰላምታ ጋር
እለቱም ቅዳሜ 15.08.2020 ነው።
ዒድ ሙባረክ!
ለመላው የእስልምና ሀይማኖት ተከታይ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እንኳን ለ1441ኛውና ለታላቁ የዒድ አል-አድሐ (አረፋ) በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ለማለት እንወዳለን። በአሉ የሰላም፣ የፍቅት፣ የአብሮነት እና የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ ከልብ እንመኛለን!
በዚህ አጋጣሚ በአሉን ስናከብር የኮረና ቫይረስ (ኮቪድ19) ወረርሽኝ የመከላከል መንገዶችን መተግበር እንዳንዘነጋ ልናስታውሳችሁ እንወዳለን።
«weniger
የተወደዳችሁ የቤተሰብ ማህበር አባሎች እንኳን ደህና ቆያችሁን!
በ Covid-19 ምክንያትና እሱን ተከትሎ በመጣው የሁሉም መዘጋጋት፣ ምንም እንኳን ለማድረግ እና ለመፈጸም ያቀድናቸውን ተግባራቶች መቶ በመቶ ለመከወን ባንችልም፣ የቤተሰብ ማህበር የቦርድ አባሎች ደከመኝና ሰለቸኝ ሳንል ያደረግናቸውንና በማከናወንም ላይ ያለናቸውን አብይት ነጥቦች ለእናንተ ለአባሎቻችን ለማሳወቅ እና ለማስተዋወቅ እንወዳለን። እነዚህ እሴቶች አሁንም ሙሉ በሙሉ እንዲሳኩ አሁንም በተጠናከረ ሁኔታ ከእናንተ ህብረት እና ጥረት ጋር እንደምናሳካቸው ምንም ጥርጥር የለንም።
1ኛ ስለ Covid-19 መረጃ በተለይ ላይፕዚግን ሚመለከቱ የመንግስት መመሪያዎችን እየተከታተልን በድህረገጽችን፣ በፌስቡክ እና በትዊተር በአማርኛ ስናቀርብ ነበር።
2ኛ Covid-19 ን ተከትሎ ህዝባችንን እና ወገናችንን ለመርዳት በሚል ባደረግነው የሁላችንም ጥረት የተሰባሰበውን 2.520,00€ ወይም 2.623.00$ ለዚህ አላማ ገቢ ከሚያሰባስቡት ድርጅቶች ውስጥ በ Global Alliance Fort the Rights of Ethiopians የከፈተውን ጎ-ፈንድ-ሚ አካውንት Support Ethiopians against COVID-19 ውስጥ በማስገባት የዜጎቻችንን ችግር በመጠኑም ለመቅረፍ በመቻላችን ኩራት ቢሰማንም አሁንም ግን ማሰስባሰባችንን እንደቀጠልን መሆናችንን ለማሳወቅ እንወዳለን።ኮሮና አሁንም አለና።
3ኛ በማህበራችን ደንብ ላይ እንደ ዋና ነጥብ አድርገን ያስቀመጥነው የጀርመንኛ ቋንቋን ለመማር ለሚፈልጉ አባሎቻችን ሁኔታዎችን ማመቻቸት መሆኑ የሚታወስ ነው። ይህንንም በተመለከተ ከ Villa- Leipzig.de (የተለያዩ በጎ አድራጊ ድርጅቶችን በስሩ የያዘ) ማህበር በመነጋገር በተለያዩ ደረጃዎች ከ A1 አንስቶ እስከ B2 ድረስ የቋንቋ ትምህርት የሚገኝበትና ከዚህም አልፎ ለፈተና አዘጋጅቶ ለማቅረብ ጥረት በማድረግ ላይ የምንገኝ ስንሆን ከላይ እንደተጠቅሰው አንድም በኮሮና የተነሳ ሁለትም አሁን የበጋ እረፍት Sommerferien በመሆኑ ውሳኔውን የሚወስኑት አካሎች ለጊዜው ስራ ላይ ባይገኙም ወደ ስራ ገበታቸው ሲመለሱ የኛን ጉዳያችን አይተው የሚያሳውቁንን ወደ እናንተ የምናደርሰው ይሆናል። እስከዛው ድረስ ግን ሁሉም የማህበራችን አባሎች ከሰኞ እስከ አርብ በቀን በተለያዩ ሶስት ፕሮግራሞች ትምህርት መውሰድ እንደሚችሉ ስናሳውቅ በደስታ ነው። ይህም ፕሮግራም ቅድመ ዝግጅት የማያስፈልገው ከመሆኑም በላይ በተለያዩ ደርጃዎች ስር የሚሰጥ በመሆኑ ማናችንንም ለማሳተፍ የሚችለድል ነው። ቦታውና የሰአቱ ፕሮግራም እንደሚከተለው ነው፤
4ኛ አሁን እንደሚታወቀው ትምህርት ቤት ዝግ መሆኑና ለተማሪዎች የእረፍት ጊዜ በመሆኑ ለአባሎቻችንና በተለይም ለልጆቻችን የመዝናኛ ፕሮግራም በማቀናጀት ጥረት Leipziger Zoo በመጎብኘት የተለየ የመዝናናትና የመማር እድል እንዲያገኙ በማህበራችን ስም እየሞከርን ያለውን ሂደት በቅርቡ መልስ ሲያገኝ እንዴትና በምን አይነት ሁኔታ ይኽንን ቀን እንደምናሳልፍ ከእናንተ ጋር በአንድነት የምንወጥነው ይሆናል። ያም ማለት ምን ያህል ሰው እና አከፋፈሉንም ይመለከታል።
5ኛ ምንም እንኳን በኮሮና ምክንያት እና በስራ ተወጥረን ያለ ቢሆንም ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆችን መርዳት እና ከጎናቸው ለመቆም ባለን ጽኑ ፍላጎት ለጊዜው በህክምና ላይ የሚገኝ/የምትገኝ አንድ ወንድማችን/እህታችንን 120 ኪሜ እየተጓጓዝን በየጊዘው እየተቀያየርን (ከቦርድ አባል ውጪ የሆኑ አባላቶቻችንንም እየጨመርን) በመመላለስ ደህንነቱን/ደህንነቷን በመጠየቅና ከ ሃኪሞቹ ጋር በመነጋገር ብቻውን አለመእሆኑን/ብቻዋን አለመሆኗን በማሳየት ላይ እንገኛለን። ይኼም ማለት ሁላችንም እንደ ቤተሰብ የምንጠያየቅ፣ የምንተሳሰብና አንዳችን ለሌላችን ደህንነት አብረን የምንቆም እንደመሆናችን የቦርዱ አባላት ብቻ ሳንሆን ሁላችንንም አሳትፎ ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን የምንንከባከብበት ሁኔታዎችን መፍጠር አስፈላጊ ነው። እስካሁንም የዘነጋናቸውና ትኩረት ያልሰጠናቸው የሚመስላቸው ወዳጆቻችንን ከውዲሁ ይቅርታ እየጠየቅን እርስ በእርስ በመነጋገርና በማስታወስ ሁሉንም የሚያሳትፍ መድረክ ለመክፈት ጥረታችን አሁንም ይቀጥላል።
6ኛ አስደሳች ዜና! የዘመን መለወጫ እንቁጣጣሽን በአንድነትና በደስታ ለማክበር በፈረንጆች አቆጣጠር September 11 2020 (አርብ) ቅድመ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ላይ የምንገኝ ሲሆን በቅርቡ ሁላችንንም የሚያሳትፍ እና የኛ የምንለውን ዝግጅት የምንፈጽምበትን ቦታና ዝርዝር ሁኔታዎችን እንደምናሳውቃችሁ ስንገልጽ በደስታ ነው።
ሃገራችንንና ህዝባችንን ፈጣሪ ይጠብቅልን
ቤተሰብ ለዘላለም!
በላይፕዚግ ከተማ የሚገኘው ቤተሰብ የኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ማህበር በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ሃዘን ይገልጻል፣ እንገልጻለን።
ከዚህ ጋር ተያይዞ በተለያዩ የሃገራችን አካባቢዎች በንጹሃን ዜጎቻችንና ወገኖቻችን በተለይም ህጻናት እና እናቶቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለው አሰቃቂ ግድያ እና እየደረሰባቸው የሚገኘው የአካል ጉዳቶች እና የንብረቶች መውደም እንዲሁም የዜጎች ያላስፈላጊ መንገላታት መሪር ሃዘን እንዳሳደረብን እና ልባችንንም እንደሰበረው ለመግለጽ እንወዳለን።
በህዝባችን መሃከል ያሉ ማንኛውም አይነት የሃሳቦች አለመግባባት እና ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ አና በውይይት ለመፍታት መሞከር እንጂ፣ ምንም አይነት ሃይልና ጉልበት መጠቀም ፍሬ ቢስ በመሆኑ መቆም ይገባዋል እንላለን። ይህንንም አስከትሎ ወገኖቻችንን በዘር፣ በብሄር እና በሃይማኖት እየነጣጠሉ፣ እርስ በእርስ ለማጋጨት የሚሞክሩ ሃገር ውስጥ ወይም በውጭ ሃገር የሚኖሩ ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች ይህንን እኩይ ተግባር እንዲያቆሙ ስንጠይቅ እያንዳንዳችንም የእነዚህ እኩይ ተግባሮች ተከታይ ላለመሆን እና ህዝብን አበጣባጭ የሆኑ ሶሺያል ሜዲያዎችን ብሎክ በማድረግ የወገናዊነት እና የሃገራዊነት ሃላፊነታችንን መወጣት እንዳለብን እናሳስባለን።
ሰላምና መረጋጋት ለምንወደው ህዝባችን።
ኢትዮጵያን እና ህዝባችንን ፈጣሪ በጥበቡ ይጠብቅልን።
«weniger
ጥሪያችንን ሰምታችሁ ለምታደርጉት አስተዋጽኦ እያመሰገንን፣ እስካሁን ከእኛ እና ከእናንተ በአጠቃላይ 2.623,00$ ወይም 2.514,79€ አሰባስበን አስተላልፈናል።
«weniger
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወንድም እህቶቻችን በሙሉ እንኳን 1441ኛው ታላቁ የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት ቤተሰብ - ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ማህበር መልካም ምኞቱን እየገለፀ፤ በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የብልፅግና፣ የመተሳሰብ እና የተቸገሩ ወገኖቻችንን የሚንዘክርበት ይሆን ዘንድ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።
ኢድ ሙባረክ
«weniger
ጥሪያችንን ሰምታችሁ ለምታደርጉት አስተዋጽኦ እሁንም በድጋሚ እያመሰገንን፣ ዛሬም ከእናንተ ያሰባሰብነውን አስተላልፈን። እስካሁን 1.908,00$ ወይም 1.839,71€ አሰባስበን አስተላልፈናል።
እሁንም ለእርስዎ በእርሶዎ ስም ወይም በማህበሩ ስም መዋጮዎን ማሰባሰባችንን እና ማስተላለፋችንን እንቀጥላለን።
«weniger
ጥሪያችንን ሰምታችሁ ለምታደርጉት አስተዋጽኦ በድጋሚ ከልብ እያመሰገንን፣ እስካሁን ከእኛ እና ከእናንተ አሰባስበን ያስተለላፍነው መዋጮ 1.778,00$ ወይም 1.714,72€ ደርሷል።
እሁንም ለእርስዎ በእርሶዎ ስም ወይም በማህበሩ ስም መዋጮዎን ማሰባሰባችንን እና ማስተላለፋችንን እንቀጥላለን።
ውድ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች፤
ጥሪያችንን ሰምታችሁ ስላደረጋችሁት አስተዋጽኦ ከልብ እያመሰገንን፣ እስክሁን በቀጥታ ሊንኩ ሳይሆን በማህበሩ ስም 1.628,00$ ወይም 1.454,09€ ሰብስበን አስተላልፈናል።
እሁንም ለእርስዎ በእርሶዎ ስም ወይም በማህበሩ ስም መዋጮዎን ማሰባሰባችን እና ማስተላለፋችንን እንቀጥላለን።
«weniger
ለውድ ሙስሊም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በሙሉ መልካም የፆም የፀሎት ወር ይሁንላችሁ።
ፆሙን የሰላም፣ የጤና፣ የበረከት ያርግልን። እንዲሁም ከዘመን አመጣሽ በሽታ እንዲጠብቀን ወደ አምላክ ዱአ የምናደርግበት የምናደርግበት ይሁን።
የተከበራችሁ ውድ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች፤
በአሁን ሰአት በአለማችን ላይ የብዙዎችን ህይወት እየቀጠፈ የሚገኘው የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) በሃገራችን እንደገባ እና በቫይረሱ ዜጎች እየተጠቁ እንዲሁም ህይወታቸው እያለፈ መሆኑ ይታወቃል።
በመሆኑም በሽታውን ለመከላከል ሲባል ዜጎች እንደ አስፈላጊነቱ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅስው የእለት ተእለት ኑሮአቸውን እንደቀደሞው ለማስቀጠል የማይችሉ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎ በዜጎች ላይ ሊደርስ የሚችለውን ሃገራዊ ችግር በመረዳት ለወገን ደራሽ ወገን ነው በሚል አንሳሽነት ሁሉም አቅሙ የፈቀደውን ስተዋጽኦ ያድርግ ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን።
ይሄን አስመልክቶ ለዚህ አላማ ገቢ ከሚያሰባስቡት ድርጅቶች ውስጥ በ Global Alliance Fort he Rights of Ethiopians የከፈተውን ጎ-ፈንድ-ሚ አካውንት Support Ethiopians against COVID-19 እዚህ ሊንኩን አስቀምጠንሎታል።
ይሄንን ሊንክ ተጠቅሞ መዋጮውን ማስለላለፍ ለማይችል ወይም ለማይፈልግ ደግሞ የኛ ማህበር „ቤተሰብ - የኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ማህበር“ ለእርስዎ በእርሶዎ ስም ወይም ስምዎ እንዳይጠቀስ ከፈለጉ በማህበሩ ስም መዋጮዎን ለማስተላለፍ ፈቃደኛ መሆናችንን ልንገልጽልዎ እንወዳለን።
«weniger
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንክዋን ለብርሃነ ትንሳኤ በስላም አደረሳቹ አደረስን እያልን በአሉ የስላም የፍቅር የአብሮንት በጋራ የምንተጋገዝበት እንዲሆን እንመኛለን::
ከሰኞ April 20 2020 ጀምሮ እስከ Mai 3 2020 ድረስ የጀርመን ግዛት ዛክሰን (Sachsen) ውስጥ በህዝብ መጓጓዣ እና ሱቆች ውስጥ አፍ እና አፍንጫ መሸፈን ግዴታ ነው። አፍ እና አፍንጫ መሸፈኛው ጭንብል የግዴታ ውዱ FFP2-ማስከ መሆን የለበትም፣ ቀላል ጨርቅ ውይም ሻል መሆን ይችላል።
በተጨማሪ የቤተክርስቲያን እገልግሎቶችም እስከ 15 ምእመናን ወይም ተሳታፊዎች ድረስ ተፈቅዷል። እስከ 15 ሰው የሚለው ገደብ ለቀብር ስነ ስርአት እና ለሰርግም ይሰራል።
https://www.spiegel.de/panorama/gesellschaft/coronavirus-sachsen-fuehrt-maskenpflicht-in-oepnv-und-einzelhandel-ein-a-a91eab20-b7c6-4881-ae10-19e15ceecbed
«wenigerየኮሮና መስፋፋትን ለመቀነስ የወጣው መመሪያ እስክ Mai 3 ተራዝሟል!
- ላይፕዚግን ጨምሮ በፈዴራል ግዛት ዛክሰን (Sachsen) ውስጥ በአሁኑ ሰአት የሚሰራው „ከቤት ያለመውጣት መመሪያ“ (Ausgangssperre bzw. -beschränkungen) ከ ሰኞ April 20 2020 ጅምሮ ይነሳል። ያማለት ከ ሰኞ ጀምሮ ቤት ለቆ ለመውጣት ምክንያት አያስፈልግም።
- በአገር ደረጃ ሚሰራው የዝዝውር ገደብ (Kontaktsperre bzw. -beschränkungen) ግን ተራዝሞ እስከ Mai 3 ድረስ ይቀጥላል። ይህ ማለት ከ April 20 በኋላም አብረው ከሚኖሩት ሰዎች ጋር ወይም ከአንድ ሌላ ሰው ጋር ብቻ ነው በአደባባይ መቆየት የሚቻለው፡፡ የሰዎች ስብስብ ላይ እገዳው አሁንም እንደጸና ይቆያል።
ከ April 20 2020 እስከ Mai 3 2020 ምን ለውጥ አለ?
- እስከ 800 ካሬ ሜትር ስፋት የሽያጭ ቦታ ያላቸውን ሱቆች መክፈት ይችላሉ፡፡ ይህ በመኪና መደብሮች፣ በብስክሌት ነጋዴዎች እና በመጻሕፍት መደብሮች ላይም ይሠራል፡፡ ለመክፈት ተጨማሪ መስፈርቶች፤ ወረፋ መኖር የለበትም፣ በ 20 ካሬ ሜትር ስፋት ውስጥ አንድ ደንበኛ ብቻ ነው መኖር ያለበት።
- ፀጉር ቤቶች ከ Mai 4 ቀን ጀምሮ መስፈርቶችን ካሟሉ መክፈት ይችላሉ። ፀጉር አስተካካዮች ጓንት፣ የፊት እና የዓይን መከላከያ በስራ ቦታ ላይ መልበስ አለባቸው፣ እንዲሁም ቀጥተኛ የሰውነት ግንኙነት መኖር የለበትም።
- ሙዚየሞች፣ የመታሰቢያ ቦታዎች፣ ቤተ መጻሕፍት፣ የዕፅዋት የአትክልት ስፍራዎች እንደገና ሊከፈቱ ይችላሉ፡፡ እዚያም ጎብኝዎች ቢያንስ 1.5 ሜትር ርቀትን መጠበቅ እና የንፅህና ደንቦችን ማክበር አለባቸው።
- ትምህርት ቤቶች ከ Mai 4 2020 ጀምሮ ቀስ በቀስ ይከፍታሉ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ለሚያጠናቅቁ ተማሪዎች ከ April 20 ጀምሮ ት/ቤቶች ክፍት ናቸው፡፡
ከ April 20 2020 እስከ Mai 3 2020 እንደተዘጋ ወይም እንደተከለከለ የሚቆዩት?
- ሆስፒታል እና የአዛውንቶች መኖሪያ (Alten- und Pflegeheime) ሰው መጠየቅ አይቻልም።
- ረጅም ጉዞዎች፣ ዘመድ ጥየቃ እና እንግድንት ባይደረግ ሲል የጀርመን መንግስት ይመክራ።
- ትላልቅ የገበያ ማዕከሎች እና የገቢያ አዳራሾች ዝግ እንደሆኑ ይቆያሉ።
- ምግብ ቤቶች እና ቡና ቤቶች እንደተዘጉ ይቆያሉ፡፡
- ትላልቅ ዝግጅቶች እስከ August 31 2020 የተከለከሉ ናቸው፡
- ቤተክርስቲያን እና እምነት ተቋማትም እስከ August 31 2020 ለመእመናን እንደተከለከሉ ይቆያሉ።
- የመዋለ ሕጻናት እንደተዘጉ ይቆያሉ።
- የግንባታ መሳሪያ ሱቆች እና የአትክልት መደብሮች (Bau- und Gartenmärkte) ለግል ደንበኞች ክፍት ሊሆኑ ሚችሉበትን ሁኔታ ዐርብ ዕለት ይገለጻል ተብሎ ይጠበቃል።
«weniger
የአማዞን (Amazon) ደንበኛ ነዎት? ከሆነ በሚቀጥለው ግዥዎ ለእኛ አንድ ጥሩ ነገር ሊያደርጉ ይችላሉ፤ በ AmazonSmile በኩል ይግዙ!
AmazonSmile ለአማዞን ደንበኞች ቀላሉ መንገድ ነው፣ ከእያንዳንዱ ግዢ ያለምንም ተጨማሪ ወጪ በጎ አድራጊ ድረጅቶችን መርዳት የሚችሉበት። የኛ ማህበር "ቤተሰብ - የኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች" እደዚሁ በ AmazonSmile ፕሮግራም ውስጥ ስለሚሳተፍ፣ ከአማዞን ግዢዎች ሊደገፍ ይችላል ማለት ነው።
ለመጀመሪያ ጊዜ smile.amazon.de ሲጎበኙ፣ ድርጅት እንዲመርጡ ይጠየቃሉ፤ ከዛ "BETESEB - Äthiopier und Freunde Äthiopiens e.V." ን ይምረጡ። እንደዛ ካደረጉ ከእያንድአንዱ AmazonSmile ውስጥ ከተደረገው ገባያ፣ አማዞን ከጠቅላላ ዋጋው 0,5 % ቱን ለ "ቤተሰብ - የኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች" የለግሳል፡፡ በእርግጠኝነት እርሶ ምንም እይነት ተጨማሪ ወጪ የለብዎትም፡፡ ለርስዎ እቃውም፣ ዋጋውም ሆነ እገልግሎቱ ልክ Amazon.de እንደሚያካሂዱት ነው።
የሚቀጥለውን የአማዞን ገበያዎት ላይ "ቤተሰብ - የኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ማህበርን" በ AmazonSmile ከግምት ቢያስገቡን በጣም ደስ ይለናል።
በላይፕዚግ ብሎም ባጠቃላይ ዛክሰን (Sachsen) ውስጥ አሁን የሚሰራው ከቤት አለመውጣት መመሪያ (Ausgangsbeschränkung) እስከ April 20 ተራዝሟል።
ስለ ክልከላው ተጨማሪ መረጃ በ 22.03.2020 ያቀረብነውን "ከዛሬ ሌሊት ጀምሮ ላይፕዚሽ ውስጥ ከቤት መውጣት ክልክል ነው" ይመልከቱ።
«weniger↪️ቫይረሱ የፕሮቲን ሞሊኪዩል በመያዙ የሚሞት ሳይሆን በራሱ ጊዜ የሚሟሽሽ ነው፡፡ የሚጠፋበትም ጊዜ የሚወሰነው በአካባቢው ባለው የሙቀትና የአየሩ እርጥበት መጠን እንዲሁም ቫይረሱ ባረፈበት ቁስ ዓይነት ነው፡፡
↪️ቫይረሱ የውጫዊ አካሉ በስብ የተሸፈነ በመሆኑ በውኃ:ሳሙና እና ተሕዋስ አጥፊ መድኃኒት በቀላሉ የሚፈረካከስ ወይም የመከላከያ ዘዴዎቹ ናቸው:: ምክንያቱም በሳሙና በሚጸዳበት ጊዜ የሚፈጠረው አረፋ የቫይረሱን ስብ ስለሚያጠፋው ነው፡፡ እጅን ሲታጠቡ ለ20-30 ሴኮንዶች መቆየት አለበት የሚባለውም ብዙ አረፋን መፍጠር ስለሚያስችል ነው፡፡ አረፋው የቫይረሱ ሽፋን የሆነውን ስብ ስለሚያሟሟው ፕሮቲን ሞሊኪዩሉ ተበታትኖ ይፈረካከሳል፡፡
(የመረጃ ምንጫችንJohn Hopkins University)
ጸረ ኮሮና አፕ (Anti Corna App) ጀርመን ውስጥ "ገና" አልተፈቀደም። በ የውሂብ ጥበቃ (Datenschutz / Data protection) ምክንያት ገና እየተወያዩበት ነው። ከተፈቀደም በፍላጎት ላይ የተመስረተ መሆን አለበት ባዮች ብዙ ናቸው::
የሚሰራው እደዚ ነው፤
ሞባይልሽ በብሉቱዝ (Buetooth) በአንድ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኙ ሌሎች ሞባይሎች ጋር ስም አልባ (anonym) እና በተመሰጠረ መንገድ (verschlusselt) ውሂብ (data) ይለዋወጡ እና ዳታው አስራ አራት ቀን ይቀመጣል ወይም ሴቭ ይደረጋል። በዚህ አስራ አራት ቀን ውስጥ አንዱ ኮሮና ቢገኝበት ለሌሎቹ ሁሉ ስም አልባ በሆነ መንገድ እንደ WhatsApp ባሉ ማህበራዊ ሜዲያዎች እንዲመረመሩ ወይም ክዋራንቴነ እንዲገቡ ማለትም ከቤት እንዳይወጡ የሚል መልእክት ይደርሳቸዋል:: ኦስትሪያ (Östereich) ውስጥ ለምሳሌ ተፈቅድዋል፣ ሲንጋፑር (Singapur) እንደውም ስም ሳይደበቅ ነው::
«wenigerጀርመን ውስጥ ሁሉም ቦታ ያለ በቂ ምክንያት ከቤት መውጣት ተከልክሏልን (Ausgangssperee) ?
ሁሉም ቦታ አልተከለከልም። ከዛክሰን (Sachsen) ውጪ በአሁን ሰአት Bayern፣ Mecklenburg-Vorpommern እና Saarland ያለ በቂ ምክንያት ከቤት መውጣት ተከልክሏል፣ ሌሎች የፌዴራል ግዛቶች ግን እስካሁን አልከለከሉም ።
ግን! ከ23.03.20 ጀምሮ በአጠቃላይ በጀርመን ውስጥ ለሁለት ሳምንት መገናኘትን ሚያግድ (Kontaktverbot) መመሪያ ጸድቋል። በዛ መሰረት አንድ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ካልሆኑ በስተቀር ከሁለት ሰው በላይ ሆኖ ውጪ በአደባባይ መገኘት አይፈቀድም። ያ ማለት ከጓደኛ ጋር ለሁለት መሄድ ይቻላል፣ ለሶስት እና ከዛ በላይ ግን አይቻልም። ከሌሎች ሰዎች ጋር ቢያንስ 1,5 ሜትር ርቀት መኖር አለበት።
ቤት ውስጥስ እንዴት ነው?
በአጠቃላይ ቤት ውስጥ ከሚኖሩት ሰዎች ውጭ ከሌሎች ሰዎች ጋር የሚደረጉ ግንኙነቶች በጣም በዝቅተኛ ደርጃ እና የግድ አስፈላጊነት ከሆነ ብቻ መሆን አለበት። ከሁለት በላይ በአደባባይ መሰባብሰብ ክልክል ነው ሚለው መመሪያ ግን ቤት ውስጥ አይሰራም። በግሩፕ ዝግጅት ወይም ፓርቲ ማድረግ ቤት ውስጥም አይቻልም።
ቅጣቱ ምን ያህል ነው?
የመገናኘት ገደቦችን እንዳይጣሱ ተቆጣጣሪ ባለስልጣናት እና ፖሊስ ክትትል ያደርጋሉ። የመመሪያዎች ጥሰት ቅጣት ሚወስኑት የፌዴራል ግዛቶች ናቸው። የመጀምሪያውን የቅጣት ካታሎግ (Busgeldkatalog) የፌዴራል ግዛት Nordrhein-Westfalen አውጥቷል። በዛ መሰረት ለምሳሌ፤
- የውጭ ምግብ ከተገዛበት 50 ሜትር ሳይርቁ መብላት፤ 50 EURO
- ከ ሁለት ሰው በላይ እንድ ላይ በአደባባይ መገኘት፤ እያንዳንዱ 200 EURO
- ከ አስር ሰው በላይ እንድ ላይ በአደባብይ መገኝት፤ የገንዘብ ቅጣት ወይም እስከ አምት አመት እስር
- ግሪል ወይም ፒክኒክ ማድረግ፤ እያንዳንዱ 250 EURO
- ሳይፈቀድ ሆስፒታል ወይም አዛውንቶች (Altenheim) ሄዶ መጠየቅ፤ 800 EURO
- ሬስቶራንት፣ ካፌ እና መጣጥ ቤቶችን መክፈት፤ 4.000 EURO
ውጪ ምን ምን ማድረግ ይፈቀዳል?
ገደቦቹ እንደተጠበቁ ሆነው መሮጥ፣ ከእራስ ልጆች ጋር መጫወት፣ ከውሻ ጋር መሄድ፣ ስፖርት እና እየተንቀሳቀሱ አየር መውሰድ ይፈቀዳል፣ ግን በግሩፕ አይደልም። ከቤት መውጣት የተከለከሉበት (Ausgangssperre) ግዛቶች ውስጥ እነዚህ እንቅስቃሴዎች መኖሪያ ቤት አካባቢ ብቻ ነው መሆን ያለባቸው። ወደ ስራ፣ ገብያ፣ ለህክምና፣ ለአስፈላጊ ቀጠሮዎች እና ፈተናዎች ብሎም ሰው ለመርዳት አሁንም ይቻላል።
ምግብ ቤቶሽስ?
ሬስቶራንት፣ ካፌ እና ባሮች ዝግ ናቸው። ከምግብ ቤት ምግብ ማስላክ ወይም ሄዶ ማምጣት ግን ይቻላል።
ሌሎች የተከለከሉ አገልግሎት ሰጪዎች፤ የጸጉር ሳሎን፣ ኮስሜትክ ሱቆች፣ ማሳዠ እና ታቱ ቤቶች፣ የህዝብ እና የግል የስፖርት ተቋማት፣ የመዋኛ ቤቶች፣ ስፖርት ስቱዲዮዎች፣ ቡና ቤቶች፣ ክለቦች፣ ጭፈራ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች፣ ቲያትር ቤቶች፣ ኦፔራ፣ የኮንሰርት ቤቶች፣ ኤግዚቢሽኖች፣ ሲኒማዎች፣ መዝናኛዎች እና የእንስሳት ፓርኮች፣ የቁማር ቤቶች እና መሸታ ቤቶች የመሳሰሉት፡፡ በአብያተ ክርስቲያናት፣ መስጊዶች እና ምኩራቦች ውስጥ መሰባሰብም የተከለከሉ ናቸው፡፡
«weniger
እንደተጠበቀው ዛክሰን (Sachsen) ውስጥ ላይፕዚሽን ጨምሮ ከዛሬ እሁድ ሌሊት ጀምሮ ያለ በቂ ምክንያት ከቤት መውጣት የተከለከለ ነው። መከልከሉ በመጀምሪያ ለ 14 ቀን ይሰራል፡፡
በዚህ ሰአት ከቤት ለመውጣት እንደ ብቂ ምክንያት ሚቆጠሩት፤
- በህይወት እና በንብረት ላይ የመጣ አደጋን ለመሸሽ
- ወደ ስራ መሄድ እና መመለስ
- ወደ ልጆች መንከባከቢያ (Kindernotbetreuung) ሜሄድ እና መመለስ
- እቃ ሚወስዱ እና ሚያደርሱ ድርጅቶች እንዲሁም ፖስታ እገልግሎት
- የ እሳት አድጋ እና ሰው የማዳን ጉዞዎች
- ወደ ሃኪም ቤት ወይም ወደ ህክምና ቀጠሮ መሄድ
- ለመኖር ሚይስፈልጉ ነገሮችን ለመግዛት (ምግብ፣ መጠጥ፣ መድሃኒት (Apotheken)፣ ድሮገሪ እንደ DM እና ROSSMANN፣ ባንክ እና Sparkassen፣ ፖስታቤት፣ ነዳጅ ማደያ (Tankstellen)፣ ልብስ ምጠቢያ ቤቶች፣ ጋዜጣ መሸጫ ኪዮስክ)
- ከባለስልጣናት፣ ከፍርድ ቤቶች ወይም ከህግ ባለሙያ ጋር ሊቀየሩ ማይችሉ ቀጠሮዎች ካሉ
- የትዳር ጓደኛዎችን ወይም የህይወት አጋሮችን ለመጎብኘት
- ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ሰዎችን እና ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ልጆች መሸኘት
- የቀብር ሥነ ሥርዓቶችን የቅርብ ዘመድ እስከ 15 እንግዶች ድረስ
- ስፖርት እና ንጹህ አየር ለማግኘት የአከባቢ እንቅስቃሴ፣ እንዲሁም የእራስን ጋርደን መጎብኘት፣ ግን ለብቻ ወይም አብሮዎት ከሚኖሩት ከቤተሰብዎ ጋር ብቻ
- ለእንስሳት እንክብካቤ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ለማድረግ።
በዚህ ሰአት ለህይወት አስፈላጊ የሆኑ ሱቆች እና አገልግሎቶች ሰጪዎች ስራቸው መስጠት ቀጥላሉ። እነሱም፤
-
ሱፐር ማርኬቶች (Supermärkte)
-
የመጠጥ መሸጫ ሱቆች
-
መድሃኒት መሸጫ ቤቶች (Apotheken),
-
ድሮገሪዎች እንደ DM፣ ROSSMANN እና MÜLLER የመሳሰሉት
-
ቤንዚን ማድያ (Tankstellen)
-
ባንክ እና Sparkassen
-
ፖስታ ቤት
-
ጋዜጣ መሸጫ
ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ ይሄንን ይጫኑ
«wenigerየኮሮና ቫይረስ መስፋፋትን ለማገድ የጀርመን ፌዴራል መንግስት እና የፌዴራል ግዛቶች ብሎም በከተማ ደረጃ የተለያዩ ውሳኔዎችን ይተላልፋሉ። ለምሳሌ ባየርን (Bayern) ወይም ድሬስደን (Dresden) በአጠቃላይ ወደውጪ መውጣት ሲከለክል (Ausgangssperre)፣ ላይፕዚግ (Leipzig) ደሞ ሰዉ በፈቃደኝነት ከቤት እንዳይወጣ ይመከራል።
በላይፕዚግ የኮሮና ቫይረስ ላለማስፋፋት ከ 20.03.2020 ጀምሮ የተለያዩ ውሳኔዎች ተላልፈዋል፣
- የተዘጉ እና የተከለከሉ፤
- ማንኛውን የህዝብ እና የግል ዝግጅቶች (ለተጨማሪ መረጃ ይሄንን ይጫኑ)
- ሬስቶራንት እና ካፌዎች
-
የፀጉር ማጠቢያ ሳሎን
-
Baumärkte እንደ OBI, HAGEBAU, ...
- ት/ቤቶች እና ሙአለህፃናቶች
- ላይብለሪዎች (Stadtteilbibliotheken)
- Volkshochschule ማንኛውም ዝግጅቶች አና ትምህርቶች
- በተጨማሪ ሆስፒታል እና የአዛውንቶች መኖሪያ (Alten- und Pflegeheime) ሰው መጠየቅ አይፈቀድም
- ያልተዘጉ፤
- ሱፐር ማርኬት (Supermärkte)
- የመጠጥ መሸጫ ሱቆች
- ፋርማሲ (Apotheken),
- ድሮገሪ እንደ DM፣ ROSSMANN እና MÜLLER የመሳሰሉት
- ቤንዚን ማድያ (Tankstellen)
- ባንክ እና Sparkassen
- ፖስታ ቤት
- ጋዜጣ መሸጫ
- እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ያለተዘጉ ክፍሎች ከፈልጉ እሁድም መክፈት እንዲችሉ ተፈቅዶላቸዋል። በመሰረቱ እሁድ መክፈት ክልክል ነበር።
ላይፕዚግ ውስጥ እንደ ድሬስደን (Dresden) ወደውጪ መውጣት ቢከለከል (Ausgangssperre)፣ ያለ በቂ ምክንያት ቤትን ለቆ መውጣት አይፈቀድም ማለት ነው። በተጨማሪ ከአምስት ሰው በላይ መሰባሰብ እይቻልም። (ለተጨማሪ መረጃ ይሄንን ይጫኑ) ቤት ለቆ ለመውጣት እንደ በቂ ምክንያት ሚቆጠሩት፤
- እራስን ከአደጋ ለማዳን
- ወደ ስራ መሄድ
- ላይ የጠቀሱት የማይዘጉ ሱቆች ለመሄድ
- ወደ ሃኪም ቤት መሄድ
- የሕይወት አጋር፣ አዛውንት ውይም በሽተኛ ለመጠይቅ
- ስፖርት እና መንቀሳቀስ (Walk) ለብቻ ወይም ከቤተሰብ አባል ጋር፣ ግን ከአምስት ያልበለጠ
- እንሰሶችን ለመንከባከብ
ነገ እሁድ 22.03.2020 ካንስለር አንጌላ ሜርክል ከየፌዴራል ግዛቶች ጋር ከተነጋገረች በኋላ፣ በጀርመን ውስጥ እንድ አይነት ውሳኔ ብቻ ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል። እሱምበላይፕዚግ የመውጣጥ ክልከላም ሊሆን ይችላል። ያ ማለት ግን ፍጹም ከቤት መውጣት አይቻልም ማለት አይደለም።
የላይፕዚግ የጤና ቢሮ ለአስቸኳይ በኮሮና ቫይረስ ጥርጣሬ የስልክ የስልክ መስመር ከፍቷል፤ 0341 - 123 6852 (täglich 7 - 19 Uhr) (ለተጨማሪ መረጃ ይሄንን ይጨኑ)
ለ ዳግማዊ ትንሳኤ ዋዜማ በ 25. April 2020 አቅደነው የነበረው ዝግጅት ከአቅማችን በላይ በሆነው በወቅታዊው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተሰርዟል።
Die für April 25. April 2020 geplante Veranstaltung müssen wir leider wegen der Ausbreitung des Coronavirus absagen.
ቤተሰብ - ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ማህበር
ከ 25.02.2020 ጀምሮ ህጋዊ ሰውነት አግኝቷል።
BETESEB - Äthiopier und Freunde Äthiopiens e.V.
wurde am 25.02.2020 im Register des Amtsgerichtes Leipzig eigetragn.
Amtsgericht Leipzig: VR 9629 ▪ Steuernummer: 232/140/19396